የአዲስ-አፍሪካ ዓለምአቀፍ ኮንቬንሽንና ኤግዚቢሽን ማዕከል አ.ማ የባለአክሲዮኖች 7ኛ መደበኛ እና 7ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባዔዎች ቅዳሜ ህዳር 22 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ በካፒታል ሆቴል እና ስፓ ይካሄዳል፡፡ በመሆኑም የአክሲዮን ማህበሩ ባለአክሲዮኖች በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ማንነታችሁን የሚገልጽ የመታወቂያ ወረቀት በመያዝ በጉባዔው ላይ እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡ የስብሰባዎቹ ረቂቅ አጀንዳዎችም የሚከተሉት ናቸው፡፡
የመደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች
1. የጉባዔውን ጽ/ቤት መሰየም
2. የመደበኛ ጉባዔውን አጀንዳ ማጽደቅ
3. የ2010 በጀት ዓመት የዲሬክተሮች ቦርድ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ማድመጥ
4. የ2010 በጀት ዓመት የውጪ ኦዲተሮችን የሂሳብ ሪፖርት ማድመጥ
5. በዲሬክተሮች ቦርድ እና በውጪ ኦዲተሮች ሪፖርት ላይ መወያየትና ማጽደቅ
6. ለሚቀጥለው አንድ ዓመት የሚያገለግል የዲሬክተሮች ቦርድ አባላትን አበል መወሰን
7. ለሚቀጥለው አንድ ዓመት የሚያገለግል የውጪ ኦዲተሮችን ክፍያ መወሰን
8. የጉባዔውን ቃለ-ጉባዔ ማጽደቅ
የድንገተኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች
1. የጉባዔውን ጽ/ቤት መሰየም
2. የድንገተኛ ጉባዔውን አጀንዳ ማጽደቅ
3. የኩባንያውን መመሥረቻ ጽሑፍ አንቀጽ 5 ን/አንቀጽ 5.2 እና 5.3 ድንጋጌዎች ማሻሻል
4. የጉባዔውን ቃለ-ጉባዔ ማጽደቅ
ማሳሰቢያ፦ በጉባዔው ላይ መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ጉባዔው ከሚካሄድበት ዕለት ሦስት የሥራ ቀናት በፊት ቦሌ መድሃኒዓለም፣ መድሃኒዓለም ህንጻ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 601 በሚገኘው የማህበሩ ጽ/ቤት በመቅረብ ለዚሁ ዓላማ የተዘጋጀውን የውክልና መስጫ ቅጽ በመፈረም ወይም በሌላ ሕጋዊ መንገድ ውክልና በተሰጠው ግለሰብ አማካይነት መሳተፍ ይችላሉ፡፡
የአዲስ-አፍሪካ ዓለምአቀፍ ኮንቬንሽንና ኤግዚቢሽን ማዕከል አ.ማ የዲሬክተሮች ቦርድ